Refugee Survey 2025
We are carrying out a Refugee Survey this year, to help the Government better understand the experiences of former refugees and their families. Data collected from the survey will help us to improve the experience of refugees resettling in New Zealand in the future.
የኒው ዚላንድ ኢሚግሬሽን (Immigration New Zealand, INZ) መንግስት የቀድሞ ስደተኞችና ቤተሰቦቻቸው ያጋጠሟቸውን ሁኔታዎች በተሻለ ሁኔታ እንዲረዳ ለመርዳት በዚህ ዓመት የሥደተኞች ዳሰሳ ጥናት እያካሄደ ነው። የቀድሞ ስደተኞች እንዴት እየሰፈሩ እንደሆነ (ለምሳሌ፦ ምን ያህል ሰዎች ሥራ እንዳገኙ፣ የትምህርት ደረጃቸው፣ ወዘተ.) የሚያሳውቅ መረጃ ቢኖረንም፣ ስለ ስደተኞቹ የግል ልምዶች የሚነግረን ምንም መረጃ የለንም። ከዳሰሳ ጥናቱ የሚሰበሰበው መረጃ ወደፊት በኒው ዚላንድ የሚሰፍሩ ስደተኞች የሚያጋጥሟቸውን ሁኔታዎች ለማሻሻል ይረዳናል።
"ይህ የዳሰሳ ጥናት ባለፉት አምስት ዓመታት በኒው ዚላንድ የሚከተሉትን ምድቦች በመጠቀም ለሰፈሩ የቀድሞ ስደተኞች እና የቤተሰብ አባላት (ከ16 ዓመት በላይ) የታሰበ ነው፦
- የስደተኞች ኮታ
- የስደተኛ የቤተሰብ ድጋፍ ምድብ
- የማህበረሰብ ድርጅት ስደተኞችን ስፖንሰር ማድረግ
- የአፍጋን ተፈናቃዮችና አስተርጓሚዎች
- የኮንቬንሽን ስደተኞች (ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ተቀባይነት ያገኙ)"
ይህን የስደተኞች ዳሰሳ ጥናት ያካሄድነው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። በዚህ ዓመት፣ ጥናቱ በሦስት ዘርፎች (ትምህርት፣ ሥራ እና ተሳትፎ) ላይ ያተኩራል እና የሚደረገውም – በ13 የተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጉሞ በበይነመረብ ላይ ነው።
የእርስዎ ድምጽ አስፈላጊ ነው – ብዙ የቀድሞ ስደተኞች እና የቤተሰብ አባሎቻቸው የዳሰሳ ጥናቱን በሞሉ ቁጥር መረጃዎቻችን የተሻለ ይሆናሉ እናም ለወደፊት ስደተኞች ያለውን ልምድ ለማሻሻል የበለጠ ያስችለናል። ጉዳዩን እንዲያሰራጩት እና በተቻለ መጠን ብዙ ሰዎች እንዲሞሉት እንድትረዱን እናበረታታችኋለን።
ተሳትፎው ሙሉ በሙሉ በፈቃደኝነት እና ማንነት የማይገልፅ ነው፤ መልሶችዎ ምስጢራዊ ሆነው የሚቆዩ ሲሆን ከስምዎ ወይም ከመገናኛ ዝርዝሮችዎ ጋር አይገናኙም።
ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎች
የዚህ የዳሰሳ ጥናት ዓላማ ምንድን ነው?
ይህ የዳሰሳ ጥናት እየተካሄደ ያለው ኢሚግሬሽን ኒውዚላንድን (INZ) እና የኒው ዚላንድ መንግስት የቀድሞ ስደተኞችን እና የቤተሰቦቻቸውን ልምድ በደንብ እንዲረዱ ለመርዳት ነው። ከዳሰሳ ጥናቱ የሚሰበሰበው መረጃ ወደፊት በኒው ዚላንድ የሚሰፍሩ ስደተኞች የሚያጋጥሟቸውን ሁኔታዎች ለማሻሻል ይረዳናል።
የዳሰሳ ጥናቱን ማን እያካሄደ ነው?
ዳሰሳ ጥናቱ የሚካሄደው በኒው ዚላንድ ኢሚግሬሽን ስም በኢፕሶስ (Ipsos) በተባለ ገለልተኛ የምርምር ድርጅት ነው።
በዳሰሳ ጥናቱ ማን መሳተፍ ይችላል?
ባለፉት አምስት ዓመታት በኒው ዚላንድ የሚከተሉትን ምድቦች ስር ለሰፈሩ የቀድሞ ስደተኞች እና የቤተሰብ አባላት ከ16 ዓመት እና ከዛ በላይ የታሰበ ነው፦
- የስደተኞች ኮታ
- የስደተኛ የቤተሰብ ድጋፍ ምድብ
- የማህበረሰብ ድርጅት ስደተኞችን ስፖንሰር ማድረግ
- የአፍጋን ተፈናቃዮች እና አስተርጓሚዎች
- የኮንቬንሽን ስደተኞች (ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ተቀባይነት ያገኙ)
ውጤቶቹ ጥቅም ላይ የሚሉት እንዴት ነው?
ውጤቶቹ ወደፊት በኒው ዚላንድ የሚሰፍሩ ስደተኞች የሚያጋጥሟቸውን ነገሮች ለማሻሻል ይረዱናል። ይህ ደግሞ ለስኬታማ ሰፈራ ትልቅ ለውጥ የሚያመጡ አገልግሎቶችን እና ድጋፎችን ማግኘት እንዳለብን ያረጋግጣል።
የእኔ መልሶች ስም-አልባ ይሆናሉ?
አዎ፣ ለጥያቄዎች የሚሰጡት መልሶች ሙሉ በሙሉ ስም-አልባ ይሆናሉ እና ከእርስዎ ጋር ሊገናኙ አይችሉም።
የእኔ መረጃ እንዴት ይጠበቃል?
እንደ ማህበራዊ ኃላፊነታችን አካል፣ ኢፕሶስ (Ipsos) የመረጃ ጥበቃ ህጎችን እና ደንቦችን ለማክበር ቆርጦ ተነስቷል። ተጨማሪ ዝርዝሮች በእኛ የመረጃ ጥበቃ እና የግላዊነት ፖሊሲ ውስጥ ይገኛሉ፦
Privacy & Data Protection — Ipsos
የዳሰሳ ጥናቱን ውጤት ማን ማግኘት ይችላል?
መልሶች በአንድ ላይ ተሰባስበው እንደ አንድ የጋራ ውጤት ይታያሉ፣ ይህም ማለት የአንድን ሰው መልሶች ከሁሉም ጥያቄዎች ለይቶ ማውጣት አይቻልም። እነዚህ ውጤቶች በኒው ዚላንድ ኢሚግሬሽን (INZ) ወደፊት የሚሰፍሩ ስደተኞች የሚያጋጥሟቸውን ነገሮች ለማሻሻል ጥቅም ላይ ይውላሉ።
የዳሰሳ ጥናቱን ለመሙላት ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?
የዳሰሳ ጥናቱን ለመሙላት 15 ደቂቃ ገደማ ይወስዳል።
መሣተፍ ግዴታ ነውን?
አይደለም፣ መሣተፍ ሙሉ በሙሉ በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ነው። ካልፈለጉ መሣተፍ የለብዎትም፣ ነገር ግን እርስዎ የሰፈራ ልምድዎ በውጤቶቹ ውስጥ እንዲካተት ለመሣተፍ ፍቃደኛ ቢሆኑ በጣም ደስ ይለናል።
ዳሰሳ ጥናቱን አስቀምጬ በኋላ ልመለስበት እችላለሁን?
አይ፣ አንዴ ከጀመሩት በኋላ ዳሰሳ ጥናቱን ማጠናቀቅ አለብዎት። በመሃል ላይ ካቆሙ፣ መልሶችዎ አይደርሱንም። ሁሉንም ጥያቄዎች መልሰው ዳሰሳ ጥናቱን አንዴ ካስገቡ መልሶችዎን መቀየር ወይም ማውጣት አይችሉም።
ዳሰሳ ጥናቱ በሌሎች ቋንቋዎች ይገኛልን?
አዎ! ዳሰሳ ጥናቱበዳሪ፣ ፋርሲ፣ ፓሽቶ፣ ዓረብኛ፣ በርማኛ፣ ስፓኒሽ፣ ሶማሊኛ፣ ኡርዱ፣ ኪንያርዋንዳ፣ ስዋሂሊ፣ ፈረንሳይኛ፣ ፑንጃቢ፣ ትግርኛ፣ አማርኛ እና እንግሊዝኛ ይገኛል።
የዳሰሳ ጥናቱን መልሶች ማን ይተረጉማል?
ትርጉሞቹ የሚከናወኑት በዩናይትድ ኪንግደም በሚገኘው የኢፕሶስ (Ipsos) የትርጉም ቡድን ነው። እነሱ ከአካባቢው ማህበረሰቦች ጋር የተገናኙ አይደሉም እና ጥብቅ የምስጢራዊ አሰራር ደንቦችን ይከተላሉ።
ዳሰሳ ጥናቱ የሚከፈተውና የሚዘጋው መቼ ነው?
ዳሰሳ ጥናቱ ሴፕቴምበር 10፣ 2025 ተከፍቶ ዲሴምበር 10፣ 2025 ይዘጋል።
የጥያቄው የወረቀት ቅጂ ማግኘት እችላለሁን?
ይህ የዳሰሳ ጥናት በአሁኑ ጊዜ በመስመር ላይ ብቻ ነው የሚገኘው፣ ነገር ግን ወደፊት በመስመር ላይ መሙላት ለማይችሉ ሰዎች አማራጮችን ልንፈልግ እንችላለን።
ውጤቱን ማየት እችላለሁን?
የኒው ዚላንድ ኢሚግሬሽን (INZ) አጠቃላይ ውጤቶቹን በተሳተፉት ማህበረሰቦች ውስጥም ጨምሮ ያጋራል።
በዚህ የዳሰሳ ጥናት ምክንያት ምን አይነት ለውጦች ሊከሰቱ ይችላሉ?
ከዳሰሳ ጥናቱ የተገኘው ውጤት ኤጀንሲዎች በሰፈራ ድጋፍ ውስጥ በጥሩ ሁኔታ የሚሰሩ ነገሮችን እና ምን አይነት ማሻሻያዎች እንደሚያስፈልጉ አስመልክቶ በተሻለ ሁኔታ እንዲረዱ ይረዳቸዋል። መረጃው አሁን ያሉ አገልግሎቶች እና ድጋፎች የተሻሉ የሰፈራ ውጤቶችን እንዲያመጡ ለማረጋገጥ እና በአገልግሎት ወይም በድጋፍ ላይ የተለዩ ክፍተቶችን ለመሙላት ያግዘናል።
ጥያቄዎች ካሉኝ ወይም እርዳታ ከፈለግኩ ማንን ማግኘት እችላለሁ?
ማናቸውም ጥያቄዎች ካሉዎት ወይም በዳሰሳ ጥናቱ ላይ ማንኛውም እርዳታ ከፈለጉ፣ እባክዎ ወደ refugeesurvey2025@mbie.govt.nz ኢሜይል ይላኩ።
refugeesurvey2025@mbie.govt.nz
ስለ ዳሰሳ ጥናቱ ተጨማሪ መረጃ ከየት ማግኘት እችላለሁ?
ስለ ዳሰሳ ጥናቱ ተጨማሪ መረጃ በዚህ ድረ-ገጽ ላይ ማግኘት ይችላሉ፦